በደቡብ ክልል በሐዋሳ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የመሬት አስተዳደር ሠራተኞችና ግለሰቦች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር እየዋሉ መሆኑን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡

 ፕሬዚዳንቱን ሊገድሉ ሞክረዋል በሚል ዕድሜ ልክ የተፈረደባቸው ተለቀቁ 

በደቡብ ክልል በሐዋሳ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የመሬት አስተዳደር ሠራተኞችና ግለሰቦች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር እየዋሉ መሆኑን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ ካለፈው አንድ ወር ጀምሮ የመሬት አስተዳደር ሠራተኞችንና ግለሰቦችን ጨምሮ 20 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ቢሆንም፣ ሁለት ግለሰቦች ግን በዋስ መለቀቃቸውን ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡ 

አሥራ አንዱ ግለሰቦች በተለይ ኃላፊዎቹ አላግባብ በሆነ መንገድ መሬት በራሳቸውና በቤተሰቦቻቸው ስም ተከፋፍለዋል በሚል ተጠርጥረው የታሰሩ መሆናቸውን፣ ሰባቱ ግን ከኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ፈቃድ ሳይኖራቸው ያላቸው አስመስለው ሲሠሩ የተገኙ መሆኑን ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡  

ሁሉም ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት እየቀረቡና ጊዜ ቀጠሮ እየተጠየቀባቸው ምርመራው እየተካሄደ መሆኑንም ምንጮች ተናግረዋል፡፡ 

በሐዋሳ ከተማ ከመሬትና ከተለያዩ አስተዳደራዊ ሥራዎች ጋር የሚገናኝ ሙስና ፈጽመዋል በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የሚውሉት ግለሰቦች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ 

ከሁለት ወራት በፊት የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ በስፋትና በጥልቀት ውይይት የተደረገበት ጉዳይ የሙስና ወንጀል መስፋፋት ሲሆን፣ በተለይ ከመሬት ጋር በተያያዘ ባለሥልጣናት ሥልጣናቸውን ተገን በማድረግ ዘመዶቻቸውንና ራሳቸውን ባለሀብት እያደረጉ መሆናቸው ተነስቶ እንደነበር ምንጮች አስታውሰዋል፡፡ 

በተያያዘ ዜና ከሁለት ዓመታተ በፊት የክልሉን ፕሬዚዳንት አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ለመግደል ታስረዋል በሚል ክስ ተመሥርቶባቸው በዕድሜ ልክ እሥራት እንዲቀጡ የተወሰነባቸው ግለሰቦች ይቅርታ ጠይቀው መለቀቃቸው ታውቋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር