POWr Social Media Icons

Saturday, September 17, 2011


አዲስ አበባ፣ጳጉሜን 5 ፣ 2003 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት አዲሱን
 ዓመት ምክንያት በማድረግ ለ 5 ሺ 671 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በተለያየ የወንጀል ድርጊት 
ተከሰው በፍርድ ማረሚያ ቤት ከቆዩ የህግ ታራሚዎች መካከል ይቅርታ የተደረገላቸው የባህሪ ለውጥ 
ያመጡና የእስራት ጊዜያቸውን ያገባደዱ ናቸው ።
የተደረገው ይቅርታ በሙስና ፣በአስገድዶ መድፈር፣ በዘር ማጥፋትና በግፍ በሰው ህይወት ማጥፋት ክስ 
ተመስርቶባቸው የተፈረደባቸውን እንደማይመለክትም አስታውቀዋል።
ይቅርታ የሚደረግላቸው ታራሚዎች ወደ ህብረተሰቡ ሲቀለቀሉ ዳግመኛ በወንጀል ድርጊት ባለመሳተፍ 
የበደሉትን ህዝብና መንግሰት መካስ እንዳለባቸው ነው የሳሰቡት።
ህብረተሰቡም ይቅርታ ለተደረገላቸው ታራሚዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።


አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ)  በደቡብ ክልል የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች 
አምና በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተደረገው የደመወዝ ማሻሻያ ጋር ተያይዞ ሊሰጠን ይገባ የነበረውን
 የስራ ደረጃ ዕድገት አላገኘንም አሉ። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሲቪል ሰርቪስ
 ቢሮ ሀላፊ አቶ አቶ ደበበ አበራ በበኩላቸው ችግሩ መሰረታዊ የአሰራር ሂደት ተግባራዊ
ሲደረግ የተከሰተ እንደሆነ ተናግረዋል።
ሰራተኞቹ ለኤፍ ቢ ሲ ሪፖርተር እንደነገሩት ከደመወዝ ጭማሪው ጋር ተያይዞ በክልሉ የመሰረታዊ
 የአሰራር ሂደት ለውጥ ተግባራዊ ቢደረግም ምደባው ችግር አለበት  ነው የሚሉት።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ሀላፊ አቶ አቶ ደበበ አበራ በበኩላቸው 
ችግሩ መሰረታዊ የአሰራር ሂደት ተግባራዊ ሲደረግ የተከሰተ እንደሆነ ተናግረዋል።
በ15 ቀናት ውስጥ ቅሬታዎቹ ምላሽ እንደሚያገኙም ነው ያስታወቁት።
በመላው ሀገራችን የሰራተኛውን ገቢና የኑሮ ውድነት ታሳቢ በማድረግ መንግስት
 በ2003 አጋማሽ ላይ ለሁሉም የመንግስት ሰራተኛ የደመወዝ ጭማሪ አድርጓል።
ይህም በሁሉም የመንግስት ሴክተር መሰሪያ ቤቶች ነው ተግባራዊ የተደረገው።
ከዚህው ጋር በታያያዘም የሰራተኛው የደረጃ እድገት በአብዛኞቹ ክልሎች ተግባራዊ ተደርጓል።
የደቡብ ክልል የመንግስት ሰራተኞች ቅሬታ አምና ተግባራዊ ከተደረገው የደመዎዝ ጭማሪ 
ጋር በተያያዘ የስራ ደረጃ አመዳደብ ጋር ይያያዛል።
ሰራተኞቹ የሚያነሷቸው ቅሬታም የስራ ደረጃ ዕድገቱ ፍትሃዊ አይደለም የሚል ነው።
 ሰራተኞቹ አሉ የሚሏቸውን ችግሮች ያነሳሉ። በሌሎች ክልሎች ተግባራዊ መደረጉንም ያነሳሉ።
ክልሉ አስቸኳይ መፍትሄ ይፈልግልን ነው የሚሉት።
አቶ ደበበ አበራ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳርና የቢሮው ሀላፊ ናቸው።
በሀገር አቀፍ ደረጃ የስራ ምዘናና አመዳደብ ጥናት እየተደረገ መሆኑን ተናገሩ።
ይህ እስኪሆን ታዲያ በክልሉ ጊዜያዊ የመሸጋገሪያ ጊዜ ጥናት ተጠናቆ የክልሉ መስተዳድር
 ደንብ አወጥቶለት ከ12 ቀናት በፊት ለሁሉም ሴክተሮች ተሰራጭቷል።    
እሳቸው እንደሚሉት አሁን ሰራተኞቹ እያነሱት የለው ጥያቄና ቅሬታ ተገቢ ነው።
ይህንን ችግር ለመፍታት ባለፉት ወራት የተለያዩ ስራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውንም እንዲሁ።
በአሁኑ ጊዜም አዲስና ይህንኑ ችግር መፍታት የሚያስችል አሰራር ተግባራዊ እንደሚደረግም ጠቁመዋል።
ሁሉም ወረዳዎችና ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሰው ሀይላቸው በሚገባና በጥንቃቄ ሰርተውና ደልድለው
 ለክልሉ እንዲልኩ ትዕዛዝ ተሰጥቷል ነው ያሉት።
በመሆኑም በዚህ ጊዜ ውስጥ ችግሩ ይፈታል ነው ያሉት።
ማንኛውም ሰራተኛ የትኛውም ቅሬታ ሲኖረው ቅሬታውን በህጉ መሰረት መግለፁ ተገቢ ነው 
ያሉት አቶ ደበበ፣ ሰራተኞቹ ስራቸውን በአግባቡ እያከናወኑ ውጤቱን እንዲጠብቁም ነው ያሳሰቡት ።
ሰራተኛው  ተግባራዊ ለሚደረገው አዲስ ምድባ ስኬትም የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
ሴክተር መስሪያ ቤቶቹም በዚህ በኩል ከፍተኛውን ሀላፊነት ስለያዙ እነሱን የድርሻቸውን ይወጡ ብለዋል።