POWr Social Media Icons

Friday, March 18, 2011


በዓይነቱና በይዘቱ ለየት ያለውን ዘመናዊ የሐዋሳ ሁለገብ ስታዲየም ግንባታ ለማስጀመር የተካሄደው የማስታወቂያ ፕሮግራም ሳምንታትን አስቆጥሯል፡፡ስራውን በተግባር ለመጀመር አንድ ነገር ቀርቶ ነበር፡፡ የሁለገብ ስታዲየሙን ግንባታ ገቢ አሰባሳቢና አስተዳደር ምክር ቤትን ማቋቋም፡፡ እሱም ባለፈው እሁድ በሐዋሳ ሃይሌ ሪዞልት እውን ሆኗል፡፡ 
ምክር ቤቱ የተቋቋመው የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የሐዋሳ ከተማ፣ የዞንና የልዩ ወረዳ አስተዳደሮች፣ ባለሐብቶች እና የሃይማኖት አባቶች በተገኙበት ነበር፡፡
የምክር ቤቱን መቋቋም ተከትሎ ግንባታውን ለማስጀመር የገቢ ማሰባሰብ ሂደቱ ምን ይሁን በሚለው ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ከተደረገ በኋላ ሐዋሳ ስታዲየም ቴሌቶን 2003 በሚል ስያሜ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የስራውን በይፋ መጀመር አብስረዋል፡፡
ለሁለገብ ስታዲየሙ ግንባታ እውን መሆን የክልሉ ህዝብ ፣ ከአገር ውስጥ እና ውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መረባረብ እንደሚጠበቅባቸው ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
28 ሄክታር መሬት ላይ ያርፋል ተብሎ የሚጠበቀው ሰታዲየሙ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ሲሆን እስከ 45 ሺህ መቀመጫ ያለው የእግር ኳስ ሜዳ፣ ዘመናዊ የአትሌቲክስ መወዳደሪያ እና ሌሎች 16 ዓይነት የስፖርት ውድድሮችን ማስተናገድ የሚችል ሜዳ ያካትታል፡፡
ለግንባታው እስከ 700 ሚሊዮን ብር ሊጠይቅ ይችላልም ተብሏል፡፡ ይህ የከልሉ ህዝብ ታሪክ የሆነው ስታዲየም ግንባታ የ56ቱም ብሄረሰቦች መገለጫ ሙዚየም በመሆኑ የዞን እና ወረዳ አስተዳደሮችም ህብረተሰቡን በማሳተፍ የበኩላቸውን ድጋፍ ለመወጣት በቁርጠኝነት ለመስራት ዘግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡


መምሪያው የማርች 8 በዓልን ከከተማው የተውጣጡ አመራሮች፣የየክፍለ ከተማው ተወካዮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በተለያዩ ዝግጅቶች አክብሮ ውሏል፡፡

ሴቶች ሕገመንግስቱ ባረጋገጠላቸው መብቶችና ጥበቃወች በመጠቀም ረገድ ከወንዶች እኩል መብት እንዳላቸው እንዲሁም ከተለያዩ ፆታን መሠረት ካደረጉ ጐጂ ልማዳዊ ድርጊቶች የመጠበቅና አገልግሎት የማግኘት መብታቸው የተጠበቀ መሆኑ በግልፅ ተደንግጓል፡፡
በዓሉ የሀገራችን ሴቶች በሕገ መንግስቱ የተረጋገጠላቸው መብቶች ለማስከበር የትግል አንድነታቸውን የሚያጠናክሩበት የተጀመረውን የሠላምና የዴሞክራሲያዊ ጐዞ እንዳይቀለበስ ለማድረግ እንዲሁም በኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊና ማሕበራዊ ዘርፎች በንቃት ተሳትፈው እና ተጠቃሚ ለመሆን ትግላቸውን የሚያጠናክሩበት ነው፡፡
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ ደምሴ ዶንጊሶ በዓሉን በንግግር ሲከፍቱ እንዳሉት በሀገሪቱ በክልሉና ሆነ በከተማው ከተመዘገቡ ፈጣን የኢክኖሚ ዕድገት የሴቶችን ተሳተፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባለፉት 20 ዓመታት በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡
ሕገ መንግስቱ መሠረት በማድረግም በክልሉ የቤተሰብ ሕግ ተሻሽሎ መውጣቱ ሴቶተ ቤተሰብን በመገንባት ረገድ እኩል መብትና ኃላፊነት እንዲሃራቸው ማድረጉ ይጠቀሳል ብለዋል፡፡
የከተማው ሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሪት ሥምረት ግርማ በበኩላቸው በዓሉ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ከማጐልበቱ በተጨማሪ ሴቶች በድንበር፣በኃይማኖት፣በቀለም፣በቋንቋ እንዲሁም በባሕል ሳይለያዩ የሚደርሱባቸውን ጭቆናና መማሎ የሚያወግዙበት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በዕለቱም ሥርዓተ ፆታና ልማት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ያለው ፋይዳ እንዲሁም የሴቶች የተደራጀ ተሳትፎና ንቅናቄ ለዕቅዱ ስኬት ያለው ሚና በሚመለከት ፁሑፍ ቀርቦ ውይይት በተሰብሳቢዎች ተደርጓል፡፡
ከዚህም ሌላ በከተማው ከሚገኙ የግልና የመንግስት ትምህርት ቤቶች ጥሩ ውጤት ላስመዘገቡ ሴቶች ሽልማት የተሰጠ ሲሆን የተለያዩ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች በመድረኩ ቀርቧል፡፡

በዞኑ የሚገኙ የሲቪል ሰርቪስ ጽሕፈት ቤቶች የ6 ወራት እንቅስቃሴ ሲገመገም ዋና አስተዳዳሪው እንዳሉት የመንግስት ተቋማት ፈጣን ልማትና መልካም አስተዳደርን ለማረጋገጥና ለማስፈን የሚያስችል አደረጃጀትና የአሰራር ሥርዓትን መዘርጋት ይጠበቅባቸዋል፡፡

በየደረጃው የሚገኙት የሲቪል ሰርቪስ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች የሠራተኛውን ነባርና ኋላ ቀር አስተሳሰብ አሰራሮችን ወደ ልማታዊና 

ዴሞክራሲያዊ መስመር ማስገባት ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

ተቋማቱም በየጊዜው የአፈፃፀም ብቃታቸውን በመፈተሽና በመለካት መገምገም እንዳለባቸው መግለፃቸውንም ከዞኑ ባሕል ቱሪዝምና 

የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፡፡