የኤርትራን መንግስት አስከፊ ስርዓት ለማስወገድ የሚያስችል አዲስ የስትራቴጂ ትግል የሚቀይስ የኤርትራ ብሄራዊ ጉባዔ ለዴሞክራሲያዊ ለውጥ ውይይት በሐዋሳ ተጀምሯል፡፡


የኤርትራ ኮሚሽን ለዴሞክራሲያዊ ለውጥ የኤርትራ ተቃዋሚ ኃይሎች ልዩነታቸውን አጥብበው የሀገሪቱን አምባገነን ስርዓት እንዲያስወግዱ ጥሪ አቀረበPDFPrintE-mail
ማክስኞ, 22 ህዳር 2011 16:23
የኤርትራ ህዝብ የጭቆና አገዛዝን በመቃወም ለበርካታ ዓመታት የታገለ ቢሆንም ከነጻነትም በኋላ በአምባገነን ስርዓት ለመገዛት ተገዷል፡፡ በውጤቱም የኤርትራ መንግስት በሚከተለው የአፈናና አገዛዝ ሀገሪቱ የሰብአዊ መብት የሚረገጥባትና ዜጎች በአፈና እና በፍርሃት የሚኖሩባት ለመሆን በቅታለች፡፡

በመሆኑም የኤርትራን መንግስት አስከፊ ስርዓት ለማስወገድ የሚያስችል አዲስ የስትራቴጂ ትግል የሚቀይስ የኤርትራ ብሄራዊ ጉባዔ ለዴሞክራሲያዊ ለውጥ ውይይት በሐዋሳ ተጀምሯል፡፡ ጉባዔው ከዚህ በፊት የተቋቋመው የኤርትራ ኮሚሽን ለዴሞክራሲያዊ ለውጥ ባለፉት 16 ወራት የደረሰበትን አፈጻፀም ይገመግማል፡፡

የኤርትራ ኮሚሽን ለዴሞክራሲያዊ ለውጥ ሊቀመንበር አምሃ ዶሞኒካ ፍትህና ዴሞክራሲ የናፈቀውን የኤርትራን ህዝብ ከአምባገነን ስርዓት የማላቀቅ ጊዜው አሁን ነው ብለዋል፡፡ በመሆኑም የስርዓቱ በርካታ ተቃዋሚዎች ልዩነታቸውን በማጥበብ የኤርትራን ህዝብ እንዲታደጉት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስትን አቋም ያቀረቡት የኢህአዴግ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን በኤርትራ ህዝብ ጫንቃ ላይ የተጫነውን አምባገነን አገዛዝ ለማስወገድ የተለያዩ የኤርትራ ተቃዋሚ ኃይሎች አመርቂ ውጤት ማግኘት አልቻሉም፡፡

በመሆኑም የተጀመረው ጉባዔ የነበሩትን ችግሮች በማስወገድ የጋራ ግንዛቤና መግባባት ላይ እንደሚደርስ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡ በኤርትራ ሰላምና ዴሞክራሲ ለማስፈን ለሚደረገው ትግልም ወንድም የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስትም አስፈላጊው ድጋፍ እንደማይለየው በጉባዔው የተለያዩ የሃይማኖት መሪዎችና የፖለቲካ ድርጅቶች ተወካዮችም መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ለ7 ቀናት በሚቆየው በኤርትራ ብሄራዊ ጉባዔ ለዴሞክራሲያዊ ለውጥ ከሁሉም የአለማችን ሀገራት የተወከሉ ኤርትራውያን ተሳታፊዎች ናቸው፡፡

Comments

  1. ጉባኤው ሀዋሳ በመሆኑ የተነሳ ምድሬ ፌደራል ከተማዋን ሞልቶታል፤ ከምሽቱ ሁለት ስዐት በሃላ ለመንቀሳቅስም አይቻልም። ምን አይነት ጣጣ ነው።

    ReplyDelete

Post a Comment

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር