በደቡብ ክልል መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከሶስት ቢሊዮን በሚበልጥ በጀት የልማት ስራ እያካሄዱ ነው

አዋሳ, ህዳር 5 ቀን 2004 (ሃዋሳ) - በደቡብ ክልል መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በመደቡት ከሶስት ቢሊዮን ብር የሚበልጥ በጀት ህብረተሱቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎች በመካሄድ ላይ መሆናቸውን የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ገለጸ፡፡አብዛኛዎቹ ድርጅቶች የሚንቀሳቀሱት በሀዋሳ ከተማ ፣በሲዳማ ፣ በወላይታ ፣ በጋምጎፋ ፣ በሀዲያና በጉራጌ ዞኖች መሆኑን አስታውቀው የልማት ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ ሁሉንም የክልሉ ህዝብ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ታፈሰ ገዳዎ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር እስከ 2015 የሚካሄዱት የልማት ስራዎች 490 ፕሮጀክቶች ናቸው፡፡
ፕሮጀክቶቹ በ202 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንደሚካሄዱ አመልክተው የልማት ስራዎቹ የሚያተኩሩት በግብርና ፣በጤና ፣በትምህርት ፣ በመጠጥ ውሃ ፣በመስኖና ሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ባላቸው ዘርፎች መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አብዛኛዎቹ ድርጅቶች የሚንቀሳቀሱት በሀዋሳ ከተማ ፣በሲዳማ ፣ በወላይታ ፣ በጋምጎፋ ፣ በሀዲያና በጉራጌ ዞኖች መሆኑን አስታውቀው የልማት ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ ሁሉንም የክልሉ ህዝብ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
አፈጻጸማቸውን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ክትትልና ቁጥጥር እንደሚካሄድ ገልጸው መንግስታዊ ያልሆኑት ድርጅቶች ለመንግስት የልማት አጋር በመሆን የአምስት አመቱን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድን ለማሰካት የበኩላቸው አስተዋጾኦ እንዳላቸ ገልጸዋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር