የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ስርጭት ለመጀመር የሚስችል ዝግጅት እያደረገ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28 (ኤፍ ቢ ሲ) የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ስርጭት
ለመጀመር የሚስችል ዝግጅት እያደረገ ነው።
በሬዲዮ ጣቢያው አስፈላጊነት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ትናንት በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የጋራ
ውይይት ተካሂዷል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ዮሴፍ ማሞ በዚሁ ወቅት እንዳሉት የማህበረሰብ ኤፍ ኤም
ሬዲዮ ጣቢያው ስርጭት ዓላማ የተቋሙን የመማር ማስተማር፣ የምርምርና
የህብረተሰብ አገልገሎት ለአካባቢው ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ነው፡፡
የህብረተሰብ አገልገሎት ለአካባቢው ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ነው፡፡
ጣቢያው ለጊዜው በ50 ኪሎ ሜትር ዙሪያ አገልግሎቱን የሚጀመር ሲሆን ቀስ በቀስም
የስርጭት አድማሱን እንደሚያስፋፋ ጠቁመዋል።
Comments
Post a Comment