የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚመጡ ተማሪዎችን በሁለተኛ ዲግሪ እንዲያሰለጥን ተመረጠ


አዲስ አበባ፣ መስከረም 10 2004 (ኤፍ ቢ ሲ)የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት 
የሚመጡ ተማሪዎችን በሁለተኛ ዲግሪ ተቀብሎ እንዲያሰለጥን ተመረጠ።        
ዩኒቨርሲቲው በሁለተኛ ዲግሪ ስልጠና ለመስጠት የተመረጠው ከዘጠኝ የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች
ጋር ተወዳድሮ ብቁ ሆኖ በመገኘቱ ነው።
የዩኒቨርሲቲው ማርኬቲንግና ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መልሰው ደጀኔ
ለኢ ዜ አ እንዳሉት ስልጠናው የሚሰጠው በ11 የተለያዩ ፕሮግራሞች ነው።
ዩኒቨርሲቲው ስልጠናውን የሚሰጠው  በአውሮፓ ታዋቂ ከሆነው ኢራስመስ ከተባለው
ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ፣ የካሪቢያንና የፓስፊክ ፕሮግራም ማዕቀፍ ጋር በመተባበር ነው።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር