የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ለከተማው አዲስ ከንቲባ ሾመ

 አዋሳ, ነሐሴ 30 ቀን 2003 (ሃዋሳ) - በደቡብ ሕዝቦች ክልል የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ሶስተኛ ዓመት የስራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባዔ ዛሬ ተጀመረ፡፡

ምክር ቤቱ ጉባኤውን ሲጀምር ለሀዋሳ ከተማ ከንቲባነት በሙሉ ድምጽ የሾማቸው አቶ ዮናስ ዮሴፍ ቀደም ሲል የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ የነበሩ ናቸው።

አዲሱ ከንቲባ ቀደም ሲልም በሲዳማ ዞን የዳሌ ወረዳ አስተዳዳሪ ፣የሲዳማ ዞን ትምህርት መምሪያ ሃላፊ በመሆን ያገለገሉ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ምክር ቤቱ ሾመቱን የሰጠው ቀደም ሲል የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ በነበሩት በአቶ ሽብቁ ማጋኔ ምትክ መሆኑም ተገልጿል፡፡

የከተማው ምክር ቤት ጉባኤ የ6ኛ መደበኛ ጉባኤውን ቃለ ጉባኤ መርምሮ በማጽደቅ በሶስት ቀናት ቆይታው በ2003 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ፣በ2004 በጀት ዓመት ዕቅድና በጀት ላይ ተወያይቶ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር