በደቡብ ክልል በተጠናቀቀው የትምህርት ዘመን በትምህርት ልማት ዘርፍ የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ የትምህርት ልማት ሰራዊቶች ተሸለሙ


አዲስ አበባ፣ መስከረም 7 2004 (ኤፍ ቢ ሲ)በደቡብ ክልል በተጠናቀቀው የትምህርት ዘመን በትምህርት ልማት ዘርፍ 
የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ከ100 በላይ የትምህርት ልማት ሰራዊቶች ተሸለሙ።
በሃዋሳ ከተማ ላለፉት ሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 17ኛው አጠቃላይ የትምህርት ጉባኤ የላቀ ውጤት
 ላስመዘገቡ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ ትምህርት ቤቶችና የትምህርት ጽህፈት ቤቶች የማበረታቻ ሽልማት
 በመስጠት ዛሬ ማምሻውን ተጠናቋል።
ለተሸላሚዎቹም የዋንጫ፣ የሜዳሊያ የቦንድና የተለያዩ ቁሳቁሶችን በሽልማት ተሰጥቷል።
የጉባኤው ተሳታፊዎች ባወጡት የአቋም መግለጫ መላውን ህብረተሰብ በላቀ ሁኔታ በማነቃቃት
 የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናትን በሙሉ ወደ ትምሀርት
 ቤት ለማምጣት በግንባር ቀደምትነት ለመንቀሳቃስ ቃል መግባታቸውን ባልደረባችን ሰለሞን ገመዳ ከሃዋሳ ዘግቧል። 

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር