ከቻይና የመጣ የልኡካን ቡድን በሀዋሳ ከተማ የተቋቋመውን የኢንዱሰትሪ መንደር ጎበኘ፡፡


ከቻይና የመጣ የልኡካን ቡድን በሀዋሳ ከተማ የተቋቋመውን የኢንዱሰትሪ መንደር ጎበኘ፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከቻይና ቾንቺን ግዛት ለመጣው የልኡካን ቡድን እንደገለጹት
 የበርካታ ብሄር ብሄረሰቦቸና ህዝቦች መኖሪያ የሆነው የደቡብ ክልል በኢንዱሰትሪ፣ ግብርናና አገልግሎት ተቋማት
 መሳተፍ ለሚፈልጉ ባለሃብቶች ዕምቅ ሃብት ይገኝበታል፡፡


በክልሉ 22 የሪፎረም ከተሞች የመሰረተ ልማት አገልገሎት የተሟላላቸው የኢንዱሰትሪ መንደሮች
መዘጋጀታቸውን ገልጸው በኢንዱስትሪ ዘርፍ መስራት ለሚፈልጉ ባለሃብቶች የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን
ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡


በክልሉ ካለው ምቹ ሁኔታ በመታገዝ ብዛት ያላቸው ባለሃብቶች መዋዕለ ንዋያቸውን አፍስሰው እየሰሩ መሆኑን ገልጸው
 በክልሉ በማንኛውም መሰክ መሰማራት ለሚፈልጉ የቻይና ባለሃብቶችን ለመቀበል የክልሉ መንግስት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡


ከቻይና የቾንቺን ግዛት የመጡት የልዑካን ቡድን ተወካይ የክልሉ መንግስት ላደረገላቸው አቀባበል አመስግነው
የቻይናው ሊፋን ኢንዱስትሪ ፓርክ በሀዋሳ የመኪና አካላት ማምረቻና መገጣጠሚያ መንደር ለማቋቋም የተለያየ
 ስራ እየተካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የቾንቺን ግዛት በርካታ ኢንዱስትሪ የሚገኙበት መሆኑ

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር