አዲስአበባ፣መጋቢት11፣2003 ትናንት ምሽት በይርጋለም ከተማና በሲዳማ ዞን ወንሾወረዳ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ።


በይርጋለም ከተማ ልዩ ስሙ አቦሶ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ትናንት ምሽት 5 ሰአት ከ8ደቂቃ ላይ የከተሰተው።
የመሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር እስኬል 4 ነጥብ 9 የተመዘገበበት መሆኑን በአዲስ አበባዩኒቨርስቲ የጂኦፊዚክስ ስፔስ ሳይንስ አስትሮኖሚ ኢኒስቲትዩት ተመራማሪ ዶክተር ኤልያስ  ሌዊ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል በሲዳማ ዞን ወንሾ ወረዳም ትናንት ምሽቱን ተመሳሳይ የመሬት መንቅጥቀጥ አደጋደርሷል።
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዴ ገቢባ ለኢዜአ እንደተናገሩት በወረዳው በሚገኙ 17 ቀበሌዎችላለፉት 10 ቀናት በተወሰነ የሰዓት ልዩነት በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ቆይቷል፡፡
ትናንት ከምሽቱ 5 ሰዓት ከ10 ደቂቃ ላይ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የወረዳውአስተዳደር ጽህፈት ቤትን ጨምሮ ከ100 የሚበልጡ የመኖሪያና የንግድ ቤቶች ፈርሰዋል።
ጉዳትየደረሳበችው ሁለት ግለሰቦችም በይርጋለምና ቦካሶ ጤና ጣቢያ ህክምና እያገኙ ሲሆን 10 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ግምት ያለውንብረትም ወድሟል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር