Posts

Showing posts from March, 2011

አዲስአበባ፣መጋቢት11፣2003 ትናንት ምሽት በይርጋለም ከተማና በሲዳማ ዞን ወንሾወረዳ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ።

በይርጋለም ከተማ ልዩ ስሙ አቦሶ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ትናንት ምሽት 5 ሰአት ከ 8 ደቂቃ ላይ የከተሰተው። የመሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር እስኬል 4 ነጥብ 9 የተመዘገበበት መሆኑን በአዲስ አበባዩኒቨርስቲ የጂኦፊዚክስ ስፔስ ሳይንስ አስትሮኖሚ ኢኒስቲትዩት ተመራማሪ ዶክተር ኤልያስ  ሌዊ ተናግረዋል። በሌላ በኩል በሲዳማ ዞን ወንሾ ወረዳም ትናንት ምሽቱን ተመሳሳይ የመሬት መንቅጥቀጥ አደጋደርሷል። የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዴ ገቢባ ለኢዜአ እንደተናገሩት በወረዳው በሚገኙ 17 ቀበሌዎችላለፉት 10 ቀናት በተወሰነ የሰዓት ልዩነት በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ቆይቷል፡፡ ትናንት ከምሽቱ 5 ሰዓት ከ 10 ደቂቃ ላይ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የወረዳውአስተዳደር ጽህፈት ቤትን ጨምሮ ከ 100 የሚበልጡ የመኖሪያና የንግድ ቤቶች ፈርሰዋል። ጉዳትየደረሳበችው ሁለት ግለሰቦችም በይርጋለምና ቦካሶ ጤና ጣቢያ ህክምና እያገኙ ሲሆን 10 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ግምት ያለውንብረትም ወድሟል።

Unusual moderate, but dangerous earthquake near Yirgalem, Ethiopia

Image
Today March 19 ,2011 at 11:09 PM earthquake happened at yirgalem its real earth quake (shake) it didn’t cause any disaster as far as I have seen it, but everybody felt it for 4 seconds. It was the longest quake I have witnessed in my life. Everything in my house was  shaking. Some books were dropped to the floor. Electric power also gone for 10 minutes .and I fell the shake at 7:57 am for 1 second again . UPDATE 20/03-01:09 UTC :  The shaking lasted for about 4 seconds. Original article

በዓይነቱና በይዘቱ ለየት ያለ ዘመናዊ ሁለገብ ስታዲየም በ700 ሚሊዮን ብር ወጪ በሐዋሳ ልገነባ ነው።

በዓይነቱና በይዘቱ ለየት ያለውን ዘመናዊ የሐዋሳ ሁለገብ ስታዲየም ግንባታ ለማስጀመር የተካሄደው የማስታወቂያ ፕሮግራም ሳምንታትን አስቆጥሯል፡፡ስራውን በተግባር ለመጀመር አንድ ነገር ቀርቶ ነበር፡፡ የሁለገብ ስታዲየሙን ግንባታ ገቢ አሰባሳቢና አስተዳደር ምክር ቤትን ማቋቋም፡፡ እሱም ባለፈው እሁድ በሐዋሳ ሃይሌ ሪዞልት እውን ሆኗል፡፡   ምክር ቤቱ የተቋቋመው የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የሐዋሳ ከተማ፣ የዞንና የልዩ ወረዳ አስተዳደሮች፣ ባለሐብቶች እና የሃይማኖት አባቶች በተገኙበት ነበር፡፡ የምክር ቤቱን መቋቋም ተከትሎ ግንባታውን ለማስጀመር የገቢ ማሰባሰብ ሂደቱ ምን ይሁን በሚለው ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ከተደረገ በኋላ ሐዋሳ ስታዲየም ቴሌቶን 2003 በሚል ስያሜ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የስራውን በይፋ መጀመር አብስረዋል፡፡ ለሁለገብ ስታዲየሙ ግንባታ እውን መሆን የክልሉ ህዝብ ፣ ከአገር ውስጥ እና ውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መረባረብ እንደሚጠበቅባቸው ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡ 28 ሄክታር መሬት ላይ ያርፋል ተብሎ የሚጠበቀው ሰታዲየሙ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ሲሆን እስከ 45 ሺህ መቀመጫ ያለው የእግር ኳስ ሜዳ፣ ዘመናዊ የአትሌቲክስ መወዳደሪያ እና ሌሎች 16 ዓይነት የስፖርት ውድድሮችን ማስተናገድ የሚችል ሜዳ ያካትታል፡፡ ለግንባታው እስከ 700 ሚሊዮን ብር ሊጠይቅ ይችላልም ተብሏል፡፡ ይህ የከልሉ ህዝብ ታሪክ የሆነው ስታዲየም ግንባታ የ 56 ቱም ብሄረሰቦች መገለጫ ሙዚየም በመሆኑ የዞን እና ወረዳ አስተዳደሮችም ህብረተሰቡን በማሳተፍ የበኩላቸውን ድጋፍ ለመወጣት በቁርጠኝነት ለመስራት ዘግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

የሴቶች ማሕበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነት እየጐለበተ መምጣቱን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች መምሪያ ገለፀ፡፡

መምሪያው የማርች 8 በዓልን ከከተማው የተውጣጡ አመራሮች፣የየክፍለ ከተማው ተወካዮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በተለያዩ ዝግጅቶች አክብሮ ውሏል፡፡ ሴቶች ሕገመንግስቱ ባረጋገጠላቸው መብቶችና ጥበቃወች በመጠቀም ረገድ ከወንዶች እኩል መብት እንዳላቸው እንዲሁም ከተለያዩ ፆታን መሠረት ካደረጉ ጐጂ ልማዳዊ ድርጊቶች የመጠበቅና አገልግሎት የማግኘት መብታቸው የተጠበቀ መሆኑ በግልፅ ተደንግጓል፡፡ በዓሉ የሀገራችን ሴቶች በሕገ መንግስቱ የተረጋገጠላቸው መብቶች ለማስከበር የትግል አንድነታቸውን የሚያጠናክሩበት የተጀመረውን የሠላምና የዴሞክራሲያዊ ጐዞ እንዳይቀለበስ ለማድረግ እንዲሁም በኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊና ማሕበራዊ ዘርፎች በንቃት ተሳትፈው እና ተጠቃሚ ለመሆን ትግላቸውን የሚያጠናክሩበት ነው፡፡ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዋና አፈ - ጉባኤ አቶ ደምሴ ዶንጊሶ በዓሉን በንግግር ሲከፍቱ እንዳሉት በሀገሪቱ በክልሉና ሆነ በከተማው ከተመዘገቡ ፈጣን የኢክኖሚ ዕድገት የሴቶችን ተሳተፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባለፉት 20 ዓመታት በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ ሕገ መንግስቱ መሠረት በማድረግም በክልሉ የቤተሰብ ሕግ ተሻሽሎ መውጣቱ ሴቶተ ቤተሰብን በመገንባት ረገድ እኩል መብትና ኃላፊነት እንዲሃራቸው ማድረጉ ይጠቀሳል ብለዋል፡፡ የከተማው ሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሪት ሥምረት ግርማ በበኩላቸው በዓሉ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ከማጐልበቱ በተጨማሪ ሴቶች በድንበር፣በኃይማኖት፣በቀለም፣በቋንቋ እንዲሁም በባሕል ሳይለያዩ የሚደርሱባቸውን ጭቆናና መማሎ የሚያወግዙበት መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በዕለቱም ሥርዓተ ፆታና ልማት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ያለው ፋይዳ እንዲሁም የሴቶች የተደራጀ ተሳትፎና ንቅናቄ ለዕቅዱ ስኬት ያለው

እየተመዘገበ የሚገኘውን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስቀጠል የመንግስት ተቋማት የተሻሉ የአሰራር ሥርዓቶችን መዘርጋት እንዳለባቸው የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አስታወቀ፡፡

በዞኑ የሚገኙ የሲቪል ሰርቪስ ጽሕፈት ቤቶች የ 6 ወራት እንቅስቃሴ ሲገመገም ዋና አስተዳዳሪው እንዳሉት የመንግስት ተቋማት ፈጣን ልማትና መልካም አስተዳደርን ለማረጋገጥና ለማስፈን የሚያስችል አደረጃጀትና የአሰራር ሥርዓትን መዘርጋት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በየደረጃው የሚገኙት የሲቪል ሰርቪስ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች የሠራተኛውን ነባርና ኋላ ቀር አስተሳሰብ አሰራሮችን ወደ ልማታዊና  ዴሞክራሲያዊ መስመር ማስገባት ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ ተቋማቱም በየጊዜው የአፈፃፀም ብቃታቸውን በመፈተሽና በመለካት መገምገም እንዳለባቸው መግለፃቸውንም ከዞኑ ባሕል ቱሪዝምና  የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፡፡

Hawassa is changing ... take a look

Image

Sidama Lodge offering different art to suit every taste

Image
Art Appreciation’s Never-ending The crowded lobby of Sidama Lodge offering different art to suit every taste, on Wednesday, March 2, 2011, with works by various artists including, from top left, Osman,Adamseged Michael, Kidist Brehane, Teferi Mekonnen, and Nebiyu Assefa. Upon entering Sidama Lodge, located on Cape Verde Street around Bole Rwanda, one meets the work of Fitsum Wubeshet, a local artist participating in his fourth exhibition at the lodge. The general theme of his work on show depicts desolate scenes of seemingly abandoned umbrellas over wheelbarrows, and stationary bajaj taxis, seemingly going nowhere in a dust blown sunny scene. He charges 4,000 Br for each of his four artworks on show. “I determine the price according to my feeling of how good it is,” Fitsum told Fortune. “I try to say something with each piece.” Along with his participating colleagues, of which the official number is 25, but Fortune counted a total of 28, there is a lot to say. Between t