የቀርከሃ ማገዶና ከሰል ቴክኖሎጂን ለማስፋፋትና ቀጣይነት ባለው የደን ልማት ዙሪያ የሚሰሩ ድርጅቶች ሰሞኑን በሲዳማ ዞን ሁላ ወረዳ የመስክ ጉብኝት ማድረጋቸው ተነገረ፡፡


መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ዘርፉ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለውና ከሚነገረው የቀርቀሃ ደን ከአንድ ሄክታር ከ10 እስከ 20 ሺህ ምርት ማግኘት ይቻላል፡፡
ይሁንና ግን ጥቅሙን በስፋት ለማስተዋወቅ እየተደረገ ካለው ጥረት ወጪ በበቂ ደረጃ ጥቅም ላይ ውሏል ማለት እንደማይቻል በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች ይገለጻል፡፡
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2009 በኢትዮጵያ መንግስትና በዓለም ዓቀፍ የቀርቀሃና ራታን ኔትወርክ (Inbar) ጋር በምስራቅ አፍሪካ ያለውን እምቅ ሃብት በተለያዩ ጥቅሞች ላይ ለማዋል የተለያ ፕሮጀክቶችን ነድፎ የቀርቀሃ ቴክኖሎጂዎችን ከዓለም ዙሪያ ለማሰባሰብ በማስረጽ ላይ መሆኑን ከንቲሪ ፕሮጀክት ማናጀሩ ዶክተር ፉጀኒሂ ገልጸዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በቻይናና ህንድ ያለውን ልምድ በአፍሪካ ማስተዋወቅ መሆኑን በማስታወስ፡፡
የዓለም አቀፉ Inbar ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኬሽ ሆጊንደር እንዳሉት ድርጅቱ በ36 ሃገሮች ላይ የሚንቀሳቀስ መሆኑን ገልጸው፤ በምስራቅ አፍሪካ ያለውን  እምቅ የቀርቀሃ ዓቅም ለማስተዋወቅ  የተለያዩ ተግባራትን እያተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በሃገሪቱ ማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስተር ከጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ኤጄንሲና ከግብርና ቢሮ ጋር እንሰራለን ይህ መሆኑ ደግሞ የተፈጥሮ ሃብትን በአግባቡ ለመጠበቅ የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ ባፈው ሁለት ዓመታት የተከናወኑ ስራዎችን በሲዳማ ዞን ሁላ ወረዳ ተገኝተው ጐብኝተዋል፡፡
በክልሉ የማዕድንና ኢነርጂ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሃጐስ አባተ በዚሁ ጉብኝት ላይ እንዳሉት የደን ውጤቶችን አብቅቶ ለማገዶ ለመጠቀም በአማካይ እስከ 30 ዓመታት የሚፈጅ ሲሆን የሚያስከትለው መዘዝም ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው፤ የቀርቀሃ ምርት ግን ከ3 ዓመት ባልዘለለ ጊዜ ውስጥ ለተለያ ጥቅም የሚደርስ በመሆኑ ቴክኖሎጂዎችን  ለማስተዋወቅ እየሰራን ነው ብለዋል፡፡
በጉብኝቱ ከኢትዮጵያና ጋና ቀርቀሃ አብቃይ ክልሎችና ከተለያዩ ድርጅቶች የተወጣጡ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ከአውሮፓ ማህበረሰብ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የሚታገዝ ነው፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር