የደቡብ ኢትዮጵያ ኮሌጅ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ያስገነባውን ስታዲየም አስመረቀ


በሐዋሳ ከተማ የደቡብ ኢትዮጵያ ኮሌጅ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ያስገነባውን ሁለገብ ስታዲየም አስመረቀ፡፡

የኒቨርስቲው ከየካቲት 12 ጀምሮ ሁለተኛውን የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የስፖርት ፌስቲቫል ውድድርንም ያካሂዳል፡፡
የከተማዋ አስተዳዳሪ ከንቲባ አቶ ሽበቁ ማጋኔ ስታዲየሙን ሲመርቁ እንደተናገሩት በውድድሩ ለመሳተፍ ለሚመጡ የልዑካን ቡድኖች የሐዋሳ ከተማ ህዝብ የተለመደውን አቀባበል በማድረግ ህብረ ብሄራዊነቷን ማሳየት አለበት፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ኮሌጅ ባለቤት አቶ ዘሪሁን ቀቀቦ በበኩላቸው ኮሌጁ ለ2ኛ ጊዜ የሚካሄደውን የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስፖርት ፌስቲቫል ለማስተናገድ ከዛሬ 6 ወር በፊት ዝግጅት መጀመሩን ተናግረዋል፡፡ ይህንን ለማሳካትም ከተለያዩ አካላት ጋር እንቅስቃሴ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
ከተለያዩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ የውድድሩ ተሳታፊዎችም በስፍራው ይገኛሉ፡፡
ለ15 ቀናት በሚቆየው ውድድር ከ22 በላይ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ይሳተፋሉ ከ1 ሺህ በላይ ስፖርቶች በእግር ኳስ፣ መረብ ኳስ፣ ቅርጫት ኳስ፣ ጠረጴዛ ቴኒስ፣ አትሌቲክስና ቼዝ ውድድሮች ደግሞ ለውድድር የቀረቡ የስፖርት ዓይነት ናቸው፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር