ስለ ጥንታዊው የሲዳማ መገበያያ ገንዘብ ዎማሻ ምን ያውቃሉ?

ሲዳማዎች የዛሬዋን ኢትዮጵያ ከመቀላቀላቸው በፊት የራሳቸው የሆነ የመገበያያ ገንዘብ እንደነበራቸው ይነገራል። በብሔሩ አጠራር ዎማሻ ተብሎ የሚታወቀው ይህ መገበያያ ገንዘብ፤ ከማሬትሬዛ ገንዘብ በፊት የነበረ ነው።


የታሪክ መዛግብት እንደሚያሳዩት ከሆነ ዎማሻ ከነሐስ የተሰራ ሳንቲም ሲሆን፤ ጠፍጣፋና ክብ ነው። የዎማሻ ክቡ ክፍል መሃሉ ላይ ክፍት ሲሆን፤ ከክቡ አንደኛው ክፍል የሚነሳ ጠፍጣፋና ሹል አካል አለው።


የሲዳማ አረጋውያን የገንዘቡን የመግዛት አቅም በተመለከተ እንደሚሉት ከሆነ፤ አንድ ዎማሻ እስከ አምስት መቶ ከብቶች የመግዛት አቅም ነበው።
ምንጭ፤ sidama@visitsidama.com

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር