የሃዋሳ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በማኬሄድ የተለያዩ ሹመቶችን አፀደቀ፡

የሃዋሳ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በማኬሄድ የተለያዩ ሹመቶችን አፀደቀ፡፡ ምክር ቤቱ በዚሁ ጉባኤው በ3 አጀንዳዎች ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡
በዚሁም መሰረት የ1ኛ ዙር 2ኛ ዓመት ስራ ዘመን የ5ኛ መደበኛ ጉባኤንና የ1ኛ ዙር 3ኛ ዓመት ስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ቃለ-ጉባኤዎችን ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡ የሹመት ሥነ-ሥርዓትም አካሂዷል፡፡
ምክር ቤቱ በዋና አፈ-ጉባኤነት እንዲመሩ የተከበሩ አቶ ደምሴ ደንጊሶን  በዋና አፈ-ጉባኤነት ሾሟል፡፡
የሃዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ሽብቁ ማጋኔ እንዳስታወቁት ከተማዋ የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦች መኖሪያና የቱሪስት መዳረሻ በመሆኗ የባህል፣ ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ እንዲዋቀር ተደርጓል ብለዋል፡፡
በዚህም መሰረት ምክር ቤቱን በዋና አፈ-ጉባኤነት ሲመሩ የነበሩትን አቶ ዘላለም ላሌን የባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ሃላፊ ሆነው እንዲሾሙ ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
ከንቲባው እንዳሉት ሹመቱ የተሰጣቸው ባላቸው የትምህርት ዝግጅትና የፖለቲካ ቁርጠኝነት መሰረት ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ተሿሚዎችም የቃለ-መሃላ ሥነ-ሥርዓት መፈፀማቸውን ባልደረባችን ታምራት ሽብሩ ዘግቧል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር