16ኛው ሃገር አቀፍ የዋና ኦዲተሮች ጉባኤ በሃዋሳ እየተካሄደ ላይ ነው፡፡

የክልለ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በጉባኤው መክፈቻ ላይ እንዳሉት ሃገሪቱ ያላትን ውስን ሃብት በአግባቡ በመጠቀም የተያያዝነውን  የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማሳካት በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ ይገባል፡፡
ለዚህም  ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ያለበት የኦዲት አሰራር ስርዓትን መከተል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በሃገሪቱ አየታዬ ያለው ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ዕድገት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የኦዲት አሰራር ስርዓቱ ተኪ የሌለው መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት መንግስት ካፀደቀው የእድገትና ትራንስፎርሜሸን እቅድ አንፃር የኦዲት ተቋማትን የትኩረት አቅጣጫዎችን በሚገባ መለየት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡
ለእቅዱ ስኬት የገቢ አሰባሰብ፣ ሥርዓት፣ የበጀት አጠቃቀምና የመንግስታዊ ተቋማትን አፈጻጸም በየጊዜው በመገምገምና የማሻሻያ ሃሳቦችን በማመንጨት ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
የደቡብ ክልል ኦዲት መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር አቶ ሳህሌ ገብሬ በበኩላቸው የኦዲት ተቋማት ያሉባቸውን ችግሮች በውል ተገንዝበው የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጉባኤው አቅጣጫ የሚያስቀምጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በጉባኤው የእርስ በርስ ተሞክሮን በማስፋት ጠቃሚ ግብዓት የሚገኝበት እንደሚሆንም አስረድተዋል፡፡
ለሦስት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው 16ኛው ሃገር አቀፍ የዋና ኦዲተሮች ጉባኤ ላይ ከሁሉም ክልሎች፣ ከአዲስ አበባና ከድሬደዋ መስተዳድሮች የተወጣጡ ዋና፣ ምክትል ኦዲተሮችና ባለድርሻ አካላት መገኘታቸውም ታውቋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር