የሀዋሳ ሐይቅ ውሃን ከብክለት ለመከላከል በሚያስችሉ መንገዶች ላይ የሚመክር ጉባኤ ተካሄደ።

የኢንዱስትሪ እድገት መጨመር በተፈጥሮ አካባቢ ላይ አሉታዊ ተጽንኦ ያሳድራል፡፡

በእድገቱ ሳቢያ በተፈጥሮ ላይ የሚደርሰውን አደጋ ለመከላከል ደግሞ በየደረጃው የሚገኘው የህብረተሰብ ክፍል ለአካባቢ ጥበቃ ትኩረት ሰጥቶ መንቀሳቀስ ይገባል፡፡

በኤስ.ኦ.ኤስ ሳህል ኢትዮጵያ የሀዋሳን ሀይቅ ከብክለት የመከላከል ፕሮጀክት ማነጀር አቶ ታደለ ባንቶ እንዳሉት ድርጅቱ ከዛሬ አንድ አመት በፊት ከኖርዌ ፕዩፕል ኤይድ በተገኘው የገንዘብ ድጋፍ ሀይቁን በቀጣዩ ሊበክሉ በሚችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ፕሮጀክት ቀርጾ ጥናት ሳያደርግ ቆይቷል፡፡

ጥናቱ በሀይቁ የውሃ ይዘት፣ ብክለት ሊያደርሱ ይችላሉ ተብለው በሚታሰቡ መንስኤዎችና መከላከያ መንገዶች ላይ ያተኮረ እንደነበር ተገልጿል፡፡  

ጥናቱ በአምስት አጢኝ ቡድኖች የተዘጋጀ ሲሆን ውጤቱ ለውይይት ቀርቧል፡፡

ከፋብሪካዎች የሚወጡ ፈሳሾችና በጥቁር ውሃ አካባቢ የሚገኘው የከባድ ብረት ኬሚካል ወደ ሀይቁ የሚደርሱበት አጋጣሚ ሊኖር ስለሚችል ከወዲሁ ጥንቃቄ ሊደረግበት እንደሚገባ አቶ ታደለ ተናግረዋል፡፡

የሀዋሳ ከተማ ውበቷን እንደጠበቀች ልትቀጥል የምትችለው የሀይቁን ቀጣይነት በማረጋገጥ ስለሆነ በሀይቁ ላይ ብክለት ሊያደርሱ የሚችሉ ነገሮችን ለመከላከል ሁሉም በጋራ ሊረባረብ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ከጥናቱ አቅራቢያዎች መካከል አንዱ የሆኑት ዶክተር በቀለ ለማ በበኩላቸው ሀይቁ ለከተማው በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ ስለሆነ አስፈላጊው ክትትልና እንክብካቤ ሊደረግለት ይገባል ብለዋል፡፡

ለዚህም በየደረጃው የሚገኘው ህብረተሰብ በሀይቁ አያያዝና በአካ ባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ እንዲኖረው ማድረግ ቀዳሚውን ስፍራ እንደሚያዝ ጠቁመዋል፡፡

ከተለያዩ አካባቢዎች የሚነሱ ቆሻሻዎች በቀጥታ ወደ ሀይቁ ከገቡ በስነ-ምህዳሩ ላይ ጉዳት ስለሚያደርሰ ቆሻሻዎችን በሀይቅ ዳር ከመጣል መቆጠብ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በቀረቡ ጥናታዊ ጽሁፎችም የአውደ ጥናቱ ተሳታፊዎች የተለያዩ ሀሳቦችን በማንሳት ተወያይተዋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር