በሲዳማ የሚገኙ ቡና አምራች አርሶ አደሮች ወቅታዊ መረጃ ማግኘት የሚያስችላቸው ስራ እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን ገለፀ፡፡

በሀዋሳ ከተማ በዘርፉ ለተሰማሩ አርሶ አደሮችና ባለሙያዎች የተዘጋጀ ስልጠና ላይ በባለስልጣኑ የትምህርት ህዝብ ግንኙነትና መረጃ አሰጣጥ የስራ ሂደት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ተስፋ እንደገለፁት በተለምዶ ሲሰራበት የቆየውን የግብይት ስርአት በወጥ መረጃ የተደገፈ በማድረግ አምራቹ ተጠቃሚ የሚሆንበት ስርአት ተዘርግቷል፡፡
የተለምዶ አሰራሩ አምራቹ ብዙ ተጠቃሚ ያልሆነበት፣ ደካማ የገበያ መረጃ ስርጭትና የገበያ መዋዠቅ የሚታይበት እንደነበር ገልፀው ባለስልጣኑ ውጤታማ የሆነ ዘመናዊ የግብይት ስርአት በመዘርጋት የግብይት ስርአቱ ወጥነት ያለው እንዲሆን ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡
ባለስልጣኑ ከክልሉ ህብረትስራና ግብይት ቢሮ ጋር በመተባበር አምራቾችን ከመጀመሪያ ደረጃ የግብይት የቡና ቅምሻ ማዕከላትና ከቡና አቅራቢ ህጋዊ ነጋዴዎች ጋር የማስተሳሰር ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የሲዳማ ዞን ቡና አምራች ወረዳዎች የሚገኙ ቡና አምራች አርሶ አደሮች ለምርታቸው ተገቢ ዋጋ እንዲያገኙ በግብይት አሰራርና ዘመናዊ የግብይት ስርአት ላይ ግንዛቤያቸውን ለማዳበር ስልጠናውን መዘጋጀቱን አቶ ጌታቸው አስታውቀዋል፡፡
ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ስልጠና ላይ ከሲዳማ ዞን ቡና አምራች ወረዳዎች የተውጣጡ አርሶ አደሮች የህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየኖች፣ የግብርና ባለሙያዎችና የመስተዳደር አካላት ተገኝተዋል ሲል ባልደረባችን በላይ ጥላሁን ዘግቧል፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/10HidTextN203.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር