የሲዳማ ባህላዊ ሙዚቃ እና ጭፈራ

የኢትዮጽያ በርካታ ባህላዊ እሴቶች የሚገኝበት አንዱ የሲዳማ ክልል በደቡብ ክልል ከሚገኘኑት ከአስራ ሶስት ዞኖች አንዱ ነዉ። በለቱ ዝግጅታችን ስለ ሲዳማ ክልል በባህላዊ ሙዚቃዉ እና ጭፈራ የሚያጫዉቱን የባህል ኤክስፐርት የለቱ እንግዳችን ናቸዉ ሌላዉ ፎክሎር ማለት ምን ማለት ነዉ?



በባህል እና በፎክሎር መካከል ምን አይነት ልዪነት አለ። ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በለቱ አንድ ምሁርን ጋብዘናል።

በደቡብ ክልል በሲዳማ ዞን ባህል ቱሪዝም እና የመንግስት ኮሚኒኬሽን መስራ ቤት ዉስጥ የባህል ጉዳይ ኤክስፐርት እንደሆኑ የገለጹልን አቶ ስለሺ ወርቅነህ ከመስሪያ ቤታቸዉ የከፍተኛ ትምህርት እድልን በማግኘት በማግኘት በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በኢትዮጽያ ስነ-ጽሁፍና የፎክሎር ትምህርት መስክ የሁለተኛ አመት የማስትሪት ተማሪ ናቸዉ። የሲዳማ ዞን ባህላዊ ሙዚቃ እና ጭፈራ በተለያዩ መከሰቻዎች ቢታይም በተለይ ዞኑ የራሱ በሆነዉ የዘመን መለወጫ በአል ማለት ፍቼ በአል እንደሚታይ ይገልጻሉ።

በአዲስ አበባ ዪንቨርስቲ የስነ-ጽሁፍ እና የፎክሎር ትምህርት መስክ ለማስትሪት ዲግሪ የሁለተኛ አመት ተማሪ የሆኑት አቶ ስለሺ ወርቅነህን መነሻ በማድረግ በዪንቨርስቲዉ የሚሰጠዉን ትምህርት አስመልክቶ የፎክሎር ትምህርት ስንል ምን ማለታችን ነዉ በማለት በዚሁ ተቋም መምህር የሆኑትን አቶ ወንዶሰን አዳነን አነጋግረናል። ያድምጡ !

http://www.dw-world.de/dw/article/0,,6190673,00.html



Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር