ለሀዋሳ ከተማ 50ኛ አመት እና ለከተሞች ቀን በአል የሚመጡትን እንግዶች...

የሀዋሳ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንትና የደቡብና የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሻለቃ ፊልሞን ጁታ በአሉን ምክንያት በማድረግ በሰጡት መግለጫ በመንግስት ምቹ የኢንቨስትመንት ፓሊሲ በመታገዝ የከተማዋን ፈጣን እድገት ወደዚህ ደረጃ በማድረስ ረገድ የነጋዴው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሀዋሳ ባሳየችው ፈጣን እድገት ደረጃቸውን የጠበቁ ውብ፣ ዘመናዊና ምቹ ሁቴሎች፣ ካፍቴሪያዎችና ሌሎችም የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲሁም መሰረተ ልማት የተስፋፉበት ከተማ ለመሆን በቅታለች፡፡

ህብረ ብሔሯ ሀዋሳ ህዳር 29 የብሄረሰቦች ቀን፣ የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ እና ሌሎችም ሀገር አቀፍ በአላትን በማስተናገድ ብቃቷ እንደምትታወቅ ፕሬዝዳንቱ ሻለቃ ፊልሞን ገልፀዋል፡፡ 

እንግዶችን በማስተናገድ ተገቢውን ልምድ ያካበቱት የደቡብ መዲና የህብረ ብሄሯ ከተማ ነጋዴዎች የሀዋሳ 50ኛ አመትና የ2003 የከተሞች ቀን ለማክበር ወደ ከተማዋ የመጡትን እንግዶች ለማስተናገድ ሁሉም በአንድነት ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ ተዘጋጅተዋል ብለዋል፡፡

ከዚህ አንጻር በመኝታ፣ በካፍቴሪያና በሆቴል አገልግሎት ያለምንም የዋጋ ጭማሪ በተገቢው በማስተናገድ የከተማዋን መልካም ስምና ገጽታ በይበልጥ ለማሳደግ በከተማው ነጋዴዎች በኩል አስፈላጊውን ዝግጅት መደረጉን ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል፡፡

ከሚመጡት እንግዶች ነጋዴው ተጠቃሚ ከመሆኑ ባሻገር እንደግዶች፣ ኢንቨስተሮችና የንግዱ ማህበረሰብ አባላትን የሚያካትት በመሆኑ ከተማዋን ለማስተዋወቅና ተጨማሪ ኢንቨስተሮችን ለመሳብ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ፕሬዝዳንቱ ጨምረው አስታውቀዋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር