የሀዋሳ ከተማ 50ኛ ዓመት በዓልና የኢትዮጵያ ከተሞች ቀንን ለማክበር አስፈላጊው ዝግጅት በመጠናቀቅ ላይ ነው፡፡

በድርብ በዓሉ ምክንያት በርካታ ቁጥር ያላቸው እንግዶች ይመጣሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡
የከተማዋ ትራንስፖርት ጽህፈት ቤትና ፖሊስ መምሪያ የትራንስፖርት ሂደቱን ለማሳለጥና ወንጀልን በጋራ ለመከላከል ይቻል ዘንድ ከባጃጂ አሽከራሪዎችና ባለሃብቶች ጋር የምክክር መድረክ አዘጋጅቷል፡፡
የሃዋሳ ከተማ ትራንስፖርት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሳሙኤል አቤቶ እንደገለጹት በከተማዋ ያለውን የትራንስፖርት ሂደት የተሳካ ለማድረግ በርካታ ሥራዎች ተሰርተዋል፡፡
በዚህ ምክንያትም በየዓመቱ የሚከሰተው የትራፊክ አደጋ ተከትሎ የሚመጣው የአደጋ ቁጥር መቀነሱን አቶ ሳሙኤል ተናግረዋል፡፡
የባጃጅ አሽከራሪዎችም ህግን በማክበር ህዝቡነ ማገልገልና የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
የሃዋሳ ከተማ ፖሊስ ወንጀል መከላከል የሥራ ሂደት አስተባባሪ ኢስፔክተር ታደሰ አሚጦ በበኩላቸው በከተማዋ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመከላከል የባጃጅ አሽከርካሪዎች ትልቅ ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
የባጃጅ አሽከርካሪ ሆነው ወንጀለኞችን የሚተባበሩ ጥቂት ግለሰቦች ቢኖሩም አብዛኛዎቹ በተገቢው መንገድ አገልግሎት የሚሰጡ በመሆኑ ህበረተሰቡ አልፎ አልፎ የሚያንፀባርቀው የተሳሳተ አመለካከት ተገቢ እንዳልሆነ ኢንስፔክተር ታደሰ ገልጸዋል፡፡
ለእግረኛ ቅድሚያ ያለመስጠት፣ ጠጥቶ ማሽከርከር፣ ትርፍ መጫን፣ በእግረኛ መንገድ መቆምና መሰል የህግ ጥሰቶች በባጃጂ አሽከርካሪዎች ላይ እንደሚታዩ ተናናገሩት፤ ሳጂን ተስፋዬ ደምሴ የሃዋሳ ከተማ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት የሥራ ሂደት አስተባባሪ ናቸው፡፡
በመሆኑም እነዚህ ችግሮች ቀርፎ ለህበረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት ይቻል ዘንድ የጋራ ምክክር መድረኩ መዘጋጀቱን ሳጂን ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡
የባጃጂ ባለንበረቶችና አሽከራሪዎች በበኩላቸው እግረኛው የማቋረጫ መስመሮችን በአግባቡ ያለመጠቀም፣ ከትምህርት ይልቅ ቅጣት ማስቀደም፣ በተፈቀደ ሰዓት እንዳይንቀሳቀሱ መደረግ፣ የዜብራ አሰማመር ችግርን እንደጥያቄ አንስተው የሚመለከታቸው አካላት መልስ ሰጥተዋል፡፡
የዚህ ዓይነቱ መድረክ በየጊዜው እንደሚካሄድ ከሃዋሳ ከተማ ትራንስፖርት ጽህፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር