በሃዋሳ ከተማ ከ41 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የማምረቻና መሸጫ ማእከላት በመገንባት ላይ ናችው

ሀዋሳ, ህዳር 11 ቀን 2003 (ሃዋሳ) - በሀዋሳ ከተማ በጥቃቅን እና አነስተኛ የልማት ዘርፍ ለተሰማሩ ሰዎች አገልግሎት የሚውሉ 41 የማምረቻና መሸጫ ማዕከላት ግንባታ በመካሄድ ላይ መሆኑን የከተማው አስተዳደር አስታወቀ፡፡
የአስተዳደሩ የልማት እቅድ ክትትል እና ግምገማ የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ አሻግሬ ኡጋ ትላንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለፁት ግንባታቸው በ41 ሚሊዮን ብር ወጪ በከተማው የተለያዩ አከባቢዎች ከተጀመሩት ከእነዚህ ማዕከላት መካከል በአሁኑ ወቅት የ14ቱ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል።
የቀሪዎቹን ማእከላት ግንባታ በተያዘው የበጀት ዓመት አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በክልሉ መንግስት፣ በከተማው አስተዳደርና በማዘጋጃ ቤቱ ወጪ የሚገነቡት እነዚሁ ማዕከላት በጥቃቅንና አነስተኛ የልማት ዘርፎች ተደራጅተው ለተሰማሩና የመስሪያና የመሸጫ ቦታ ችግር ላለባቸው ከ3 ሺህ በላይ አንቀሳቃሾች ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አስረድቷል።
በተጨማሪም ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም በተገኘ ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ 3 የከብት ማድለቢያ እና የዶሮ እርባታ ማዕከላት መሰማራታቸውን ተናግረዋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር